የልጆች አገልግሎት
የልጆች አገልግሎት እድሜያቸውን ያገናዘበ ተገቢው የእረኝነት እንክብካቤ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።እድሜያቸው የደረሰ ልጆች ተገቢውን የደቀ መዝሙር የክትትል ትምህርት እንዲያገኙ ይተጋል፣ ለተግባራዊነቱም ተገቢውን ጥረት ያደርጋል። ልጆች በቤተ ክርስቲያን እንክብካቤ ሥር እያሉ ከሚያጋጥም ችግር ለመታደግ ሽፋን ይሰጣል፣ እንክብካቤው በቦታው ሳያሰልስ መሰጠቱን ያረጋግጣል። እድሚያቸውን ያገናዘበ ካሪኩለም ቀርጾ መንፈሳዊ እንክብካቤ እንዲያገኙ ያለሰለሰ ጥረት ያደርጋል። የልጆችን ስሜት የሚረዱ አገልጋዮችን በቦታው ላይ በመመደብ አገልግሎቱ ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን ይወጣል። በመሆኑም የልጆች አገልግሎት ሕልም «ወንጌል ሳይበረዝ እንዲቀጥል፣ ልጆችን በሁለንተናዊ እይታቸውና ተልእኳቸው እንዲጎለብቱ የማስቻል አገልግሎት ይፈጽማል።