Service Times: Sundays 10 am - 1 pm

የቤተሰብ አገልግሎት

እግዚአብሔር በምድር ያቋቋመው ወሳኝ ድርጅት ቤተሰብ ነው። የቤተሰብ አገልግሎት ስለ ትዳርና ቤተሰብ አስተዳደር ተገቢውን ግንዛቤ መስጠት ነው። የትዳር መሥራች እግዚአብሔር ለቤተሰብ ያለውን ዕቅድ በማስገንዘብ የቤተሰብ አባላት ለጤናማ ግንኙነት የበኩላቸውን እንዲወጡ ተገቢውን እገዛ ማመቻቸት ቀዳሚ ሚናው ነው። ምሳሌነት ያለው ቤተሳባዊ ሕይወት ምን እንደሚመስል በማሳየት ለተግባራዊነቱ የአጥቢያይቱን ቤተሰቦች ማንቀሳቀስ የአገግሎቱ ትኩረት ነው። ጤናማ ቤተሰብን የሚያጎለብቱ መርሆች እንዲሠርጹ በመስኩ ያሉ ምሁራን የሚሰጡትን ገንቢ ሃሳብ ከአጥቢያይቱ የቤተሰብ አባላት ጋር ለማስዋወቅ የቤተሰብ መነቀቂያ ማዘጋጀት ወቅታዊ ተግባራዊ እርምጃቸው ነው። በተጨማሪም ወጣቶች የጤናማ ቤተሰብ ፈለግ እንዲከተሉ የልምድ ልውውጥ የሚደረግበትን ምቹ ሁኔታ በማሰናዳት የጋብቻ ትምህርት ስልጠናዎችን በተከታታይ ማዘጋጀትና ተፈጻሚነቱንም መከታተል የአገልግሎቱ የተግባር እርምጃ ነው። «ሁሉም በደረጃው እንዲሆን ጤና፣ ክርስቶስ ተኮር ሕይወት እናጎልብት የጠንካራ ቤተሰብ መሠረት ነውና፡፡» በሚል እሳቤ ይመራል።