Service Times: Sundays 10 am - 1 pm

ሚሲዮናዊ ተልዕኮ

በወንጌል ያልተደረሱ ሕዝቦችን ለይቶ ለማወቅ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ፣ መልእክተኞች እንዲላኩ የምልጃ ጸሎት እያደረገ መልእክተኞች የሚላኩበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በተጨማሪም በወንጌል ያልተደረሱት ሕዝቦች የሚደረሱበት ስልት እየቀየሰ በትግበራው ጉዳይ ይተጋል። ሚሲዮናዊ ተልእኮ እንዲጎልበትና የሚላኩትን ለማደራጀት ተገቢውን ስልጠና ያቀናጃል ይተገብራል። በየጊዜውም ለአጭርና ለረጅም ጊዜ ሚሲዮናዊ ተልእኮ ተሳታፊዎችን ለሚመለመሉበትና በተግባር ለሚሳተፉበት ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ይንቀሳቀሳል። በተጨማሪም ሚሲዮናዊያንንና ግብአቶችን በተገቢው መንገድ ለማስተሳሰር አስፈላጊውን የማንቀሳቀስ ሥራ ይሠራል። አውራ ትኩረቱም «መልእክቱን ወዳልተደረሱ ሕዝቦች ለማድረስ፣ ሚሲዮናዊ ተልእኮን ማእከል አድርገን እንንቀሳቀስ» የሚል ነው።